የባለአክሲዮኖች ስብሰባ
ፍያብ ሪል ስቴት በ 16/6/2016 ዓ. ም በሂልተን ሆቴል የባለ አክሲዮኖች ስብሰባ ያካሄደ ሲሆን በስብሰባዉም ላይ የድርጅቱ አመታዊ እቅድ፤ የግንባታ ሂደት ሪፖርት፣ በዚህ ዓመት የተከናወኑ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የፋይናንስ ሪፖርት ለባለ አክሲዮኖች ቀርበዋል፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በነባር ባለአክሲዮኖች ጥያቄ መሰረት የአክሲዮን ሽያጭ ወደ አዲስ ገዥ ከመቅረቡ በፊት ነባር ባለ አክሲዮኖች ተጨማሪ አክሲዮን እንዲገዙ ዕድሉ ቢመቻች የሚለዉን ሃሳብ ድርጅቱ ተቀብሎ ነባር የባለ አክሲዮን ባለቤቶች አክሲዮናቸዉን እንዲያሳድጉ ጥሪዉን አቅርቧል፡፡ ስብሰባዉ ላይ የተገኙ ባለ አክሲዮኖችም አሁን ላይ ያለዉ የድርጅቱ የስራ ሂደት ጥሩ እንደሆነ፤ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያዉም ትክክለኛ ዉሳኔ መሆኑን እና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሃሳባቸዉን ገልፀዋል፡፡